About Dagu Ethiopia
Truth. Media. Society.
Dagu Ethiopia is an independent newspaper covering Ethiopia: politics, economy, society, culture and current affairs. We publish in English and Amharic, online and in print editions that are available in full as PDF.
Our mission
Truth is the beginning of every story. Dagu is rooted in the Ethiopian tradition of exchanging information and sharing what matters. We bring that spirit to independent journalism — with context, clarity and respect for our readers.
What we cover
Politics and governance, the economy and business, society and public life, culture, sport, the environment and humanitarian stories, with a focus on how events affect ordinary people.
How we work
Facts first, sources named wherever possible, and corrections published promptly. Read our editorial policy for the standards we hold ourselves to, and meet the team behind the reporting.
Contact us
Address:
Bole County 07, H.N 534
Addis Ababa, Ethiopia, 1000
Phone:
911 262 881
704 052 881
Email:
info@dagunews.com.et
Send us news tips, corrections, advertising enquiries or feedback.
ስለ ዳጉ ኢትዮጵያ
እውነት። ሚዲያ። ማኅበረሰብ።
ዳጉ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ ሕይወት፣ ባህልና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚዘግብ ነፃና ገለልተኛ የዜና ሚዲያ ነው። ዜናዎችንና ትንታኔዎችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ ለአንባቢዎቹ ያቀርባል።
ይዘቶቻችንን በዲጂታል መድረኮችና በሕትመት አማራጮች እናሰራጫለን። እያንዳንዱ የሕትመት ውጤትም በPDF ቅርጽ ለአንባቢዎች ይቀርባል።
ተልዕኳችን
እውነት የጋዜጠኝነት መሠረት ነው። ዳጉ የሚለው ስምም መረጃን የመለዋወጥ፣ የተለያዩ አመለካከቶችን የማጋራትና ለማኅበረሰቡ ጠቃሚ የሆነውን የማድረስ የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴትን ይወክላል።
ይህንን መንፈስ በነፃና በሙያዊ ጋዜጠኝነት እንተገብራለን። እውነታን በማረጋገጥ፣ ጉዳዮችን ከተገቢው አውድ ጋር በማቅረብ፣ ግልጽነትን በመጠበቅና የአንባቢዎቻችንን እምነት በማክበር ሕዝቡ በተረጋገጠ መረጃ ላይ የተመሠረተ አመለካከት እንዲይዝ እንሠራለን።
የምንዘግባቸው ጉዳዮች
ዳጉ ኢትዮጵያ በተለያዩ የሕዝብ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። ከእነዚህም፦
- ፖለቲካና አስተዳደር
- ኢኮኖሚና ንግድ
- ማኅበራዊ ጉዳዮችና የሕዝብ ሕይወት
- ባህልና ታሪክ
- ስፖርት
- አካባቢና የአየር ንብረት
- ሰብዓዊ መብቶችና ሰብዓዊ ዕርዳታ
ክስተቶችን ከመዘገብ ባለፈ፣ እነዚህ ጉዳዮች በተራው ዜጋ፣ በማኅበረሰቡና በአገሪቱ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለማሳየት እንጥራለን።
የአሠራር መርሆቻችን
በዳጉ ኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት አሠራር ውስጥ እውነታን ማረጋገጥ፣ ገለልተኝነትን መጠበቅና ለሕዝብ ጥቅም መሥራት ቀዳሚ መርሆቻችን ናቸው።
- እውነታና ማረጋገጥ፦ የምናቀርበው መረጃ በተቻለ መጠን ከታመኑ ምንጮች የተገኘና የተረጋገጠ እንዲሆን እንጥራለን።
- ገለልተኝነት፦ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በሌሎች ውጫዊ ጫናዎች ሳንመራ፣ ለሕዝብ ጥቅም የሚያገለግል ዘገባ እናቀርባለን።
- ግልጽነት፦ የመረጃ ምንጮቻችንን በሚቻልበት ጊዜ እንጠቅሳለን፤ መረጃ ገና ያልተረጋገጠ ከሆነም ይህንኑ በግልጽ እናሳውቃለን።
- ተጠያቂነት፦ ስህተት ሲፈጠር በፍጥነት እናርማለን፤ ማስተካከያዎችንም ለአንባቢዎቻችን በግልጽ እናሳውቃለን።
- ለማኅበረሰቡ ክብር፦ የሰዎችን ክብር፣ መብትና ደኅንነት በማክበር በኃላፊነት እንዘግባለን።
ስለምንከተላቸው የጋዜጠኝነት መርሆችና የአሠራር መመዘኛዎች የበለጠ ለማወቅ “የአርትዖት ፖሊሲያችንን” ያንብቡ። ከዘገባዎቻችን ጀርባ ስላለው ቡድን ለማወቅም “የቡድን ገጻችንን” ይጎብኙ።
ያግኙን
ከዳጉ ኢትዮጵያ ጋር ለመገናኘት፣ የዜና ጥቆማ ለመላክ፣ ስህተት ለማሳወቅ፣ የማስታወቂያ ጥያቄ ለማቅረብ ወይም አስተያየት ለመስጠት ከታች ያሉትን አድራሻዎች ይጠቀሙ።
አድራሻ፦
ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 534
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ 1000
ስልክ፦
0911 262 881
0704 052 881
ኢሜይል፦
info@dagunews.com.et