Dagu Ethiopia

Editorial policy

The standards we hold ourselves to.

Accuracy and verification

We publish facts we have checked. Where we cannot independently verify a claim, we say so clearly and attribute it to its source. We distinguish between what is confirmed, what is alleged and what is unknown, especially when reporting on conflict, where access is limited.

Sources

We name our sources wherever we can. We may withhold a name when a source faces a real risk of harm, and then we describe how the person knows what they told us. We do not publish information from anonymous sources unless we have good reason to trust it and, where possible, a second confirmation.

Corrections

When we get something wrong, we correct it promptly and openly, and we note the correction on the article. To report an error, write to info@dagunews.com.et with the article link and what you believe is wrong.

Independence

Our reporting is editorially independent. We do not accept payment to publish or suppress a story. Staff must disclose, and step back from, stories where they have a personal or financial interest.

News, analysis and opinion

We separate news reporting from analysis and opinion, and we label opinion as such.

Advertising

Advertisements are labelled “Advertisement” and never influence our reporting.

Photographs and credits

Photographs carry a credit and a caption where known. We do not alter images in ways that mislead readers.

Fairness and respect

We give people and organisations we report on a fair chance to respond. We treat the people in our stories, and our readers, with dignity.

Feedback and complaints

Write to info@dagunews.com.et or call 911 262 881. We read every message and respond to complaints about accuracy and fairness.

የአርትዖት ፖሊሲ

ለምንሠራው የጋዜጠኝነት ሥራ የምንከተላቸው መርሆዎች

1. ትክክለኛነትና ማረጋገጥ

የምናትመው መረጃ በተገቢው መንገድ የተጣራ መሆኑን እናረጋግጣለን። አንድን የመረጃ ወይም የዜና ዘገባ በራሳችን ማረጋገጥ በማንችልበት ጊዜ፣ ይህንኑ በግልጽ እናሳውቃለን ፤ መረጃውንም ከምንጩ ጋር እናያይዛለን። በተለይም የግጭት ዘገባዎችን በምንሠራበት ወቅት፣ የተረጋገጠውን፣ የተነገረውን ክስ እና ገና ያልታወቀውን መረጃ በግልጽ እንለያለን።

2. የመረጃ ምንጮች

በምንችልበት ሁሉ የመረጃ ምንጮቻችንን በስም እንጠቅሳለን። የምንጩን ማንነት መግለጽ ለእሱ የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ከሆነ፣ ማንነቱን ልንደብቅ እንችላለን። በዚህ ሁኔታ ግን ምንጩ መረጃውን እንዴት እንዳገኘ እናብራራለን። ለማይታወቁ ወይም ስማቸው ለማይገለጽ ምንጮች የምንሰጠው እምነት በቂ ምክንያት ሲኖረን ብቻ ነው። ከተቻለም መረጃውን ከሁለተኛ ምንጭ ጋር በማጣራት እናረጋግጣለን።

3. ስህተቶችን ማረም

በዘገባዎቻችን ላይ ስህተት ሲፈጠር፣ በአፋጣኝና ግልጽ በሆነ መንገድ እናርማለን። በተስተካከለው ዘገባ ላይም ስለተደረገው ማስተካከያ ማስታወሻ እናሰፍራለን።

በዘገባዎቻችን ላይ የተፈጠረ ስህተት ለማሳወቅ፣ የዜናውን ሊንክ እና ስህተት ነው ብለው ያመኑበትን ነጥብ በመግለጽ info@dagunews.com.et ላይ ያግኙን።

4. ነፃነት

የዜና ዘገባዎቻችን ከፖለቲካዊ፣ ከንግድና ከሌሎች ውጫዊ ተጽዕኖዎች ነፃ ናቸው። አንድን ዘገባ ለማሳተምም ሆነ ላለማሳተም ክፍያ አንቀበልም። ሠራተኞቻችን ከሚሠሩት ዘገባ ጋር የግል ወይም የገንዘብ ጥቅም ግንኙነት ካላቸው፣ ይህንኑ የመግለጽና ከዘገባው ሥራ ራሳቸውን የማግለል ግዴታ አለባቸው።

5. ዜና፣ ትንታኔና አስተያየት

የዜና ዘገባዎችን፣ ትንታኔዎችንና አስተያየቶችን በግልጽ ሁኔታ እንለያለን። በተለይም በአስተያየት መልክ የሚቀርቡ ጽሑፎች የአስተያየት ይዘት መሆናቸውን በግልጽ እናመለክታለን።

6. ማስታወቂያ

ሁሉም የማስታወቂያ ይዘቶች በግልጽ ሁኔታ «ማስታወቂያ» ተብለው ይለያሉ። ማስታወቂያዎች በዜና ዘገባዎቻችን፣ በአርትዖት ውሳኔዎቻችንና በጋዜጠኝነት ነፃነታችን ላይ ምንም ተጽዕኖ አያሳድሩም።

7. ፎቶግራፎችና የፎቶ መረጃዎች

የምናትማቸው ፎቶግራፎች የፎቶ አንሺውን ስም እና ተዛማጅ የፎቶ መግለጫ በሚታወቅበት ጊዜ ይይዛሉ። አንባቢዎችን ሊያሳስቱ በሚችሉ መንገዶች ፎቶግራፎችን አንቀይርም፤ የምስሉን እውነታና ትርጉም የሚያዛቡ ማስተካከያዎችንም አናደርግም።

8. ፍትሐዊነትና አክብሮት

በዘገባዎቻችን ውስጥ ስለምንጠቅሳቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች የምንዘግበውን ጉዳይ እንዲመልሱና የራሳቸውን አቋም እንዲያቀርቡ ተገቢውን ዕድል እንሰጣለን። በዘገባዎቻችን ውስጥ የሚካተቱ ሰዎችንም ሆነ አንባቢዎቻችንን በክብርና በሰብዓዊነት እንመለከታለን።

9. አስተያየትና ቅሬታ

ከአንባቢዎቻችን የሚቀርቡ አስተያየቶችንና ቅሬታዎችን በትኩረት እንቀበላለን። በዘገባዎቻችን ትክክለኛነትና ፍትሐዊነት ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በተለይ በጥንቃቄ እንመረምራለን፤ ለሁሉም መልዕክቶችም ምላሽ ለመስጠት እንጥራለን።

ለአስተያየትና ለቅሬታ በሚከተሉት አድራሻዎች ሊያገኙን ይችላሉ፦