About
Dagu Ethiopia is an independent newspaper covering Ethiopia: politics, economy, society, culture and more. Our motto is truth, media and society.
How we work Facts first, sources named, and corrections published promptly. Every edition is available in full as a PDF.
Advertising Ads are labelled “Advertisement” and never influence our reporting.
ዳጉ ኢትዮጵያ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበረሰብና ባህል የሚዘግብ ነጻ ጋዜጣ ነው። መሪ ቃላችን እውነት፣ ሚዲያና ማህበረሰብ ነው።
አሠራራችን መጀመሪያ እውነታ፣ ምንጮቻችንን እንጠቅሳለን፣ ስህተቶችንም በፍጥነት እናርማለን። እያንዳንዱ እትም በPDF ሙሉ ይገኛል።
ማስታወቂያ ማስታወቂያዎች “ማስታወቂያ” ተብለው ይሰየማሉ፤ በዘገባችን ላይ ተጽዕኖ የላቸውም።
Add your founding year, editor and team here. / የተመሠረተበትን ዓመት፣ አዘጋጁንና ቡድኑን እዚህ ይጨምሩ።
Contact
Send us tips, corrections, advertising enquiries or feedback. Addis Ababa, Ethiopia.
Address: Bole County 07, H.N 534 Addis Ababa, Ethiopia, 1000
Phone: 911 262 881 704 052 881
Email: info@dagunews.com.et
ጥቆማ፣ እርማት፣ የማስታወቂያ ጥያቄ ወይም አስተያየት ይላኩልን። አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።
አድራሻ፦ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 534 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ 1000
ስልክ፦ 911 262 881 704 052 881
ኢሜይል፦ info@dagunews.com.et
Send message
Privacy policy
Last updated October 23, 2026. Template: review it before relying on it. / ይህ ናሙና ነው፤ ከመጠቀምዎ በፊት ይመርምሩት።
What we collect Only what you send us: your email if you subscribe, and details in messages you write. We do not require accounts.
How we use it To send the editions you asked for and to reply to you. We do not sell your data.
Cookies and ads If we show ads from an ad network, that provider may use cookies to show relevant ads. You can control cookies in your browser.
Your choices Unsubscribe any time, or ask us to delete your data by contacting us.
Other sites and children We link to sites we do not control. Our service is not directed at children.
የምንሰበስበው እርስዎ የሚልኩልንን ብቻ ነው፦ ከተመዘገቡ ኢሜይልዎን፣ እና በመልዕክትዎ ውስጥ የጻፉትን። መለያ (account) አንጠይቅም።
እንዴት እንጠቀምበታለን የጠየቁትን እትም ለመላክና ለመመለስ ነው። መረጃዎን አንሸጥም።
ኩኪዎችና ማስታወቂያ ከማስታወቂያ አውታረ መረብ ማስታወቂያ ካሳየን፣ አቅራቢው ተገቢ ማስታወቂያ ለማሳየት ኩኪዎችን ሊጠቀም ይችላል። ኩኪዎችን በአሳሽዎ መቆጣጠር ይችላሉ።
ምርጫዎ በማንኛውም ጊዜ መውጣት ወይም መረጃዎ እንዲሰረዝ እኛን በማነጋገር መጠየቅ ይችላሉ።
ሌሎች ድረ ገጾችና ልጆች እኛ ወደማንቆጣጠራቸው ድረ ገጾች አገናኝ እናስቀምጣለን። አገልግሎታችን ለልጆች የተዘጋጀ አይደለም።
Back to home
ሬሚታንስ ፡ የውጭ ሀገር ርዳታና ኢንቨስትመንትን በልጦ የኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ገቢ ምንጭ ሆነ ኢክራም መሀመድ · 2026-11-09
አዲስ አበባ: ከውጭ ሀገራት በኢትዮጵያውያን የሚላከው ገንዘብ ለኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት አመለከተ።
በሪፖርቱ መሠረት፣ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚልኩት ገንዘብ 7.1 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ከአገሪቱ አጠቃላይ የውስጥ ምርት (GDP) 4.5 በመቶ ያህሉን ይይዛል።
በተመሳሳይ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት 4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮች የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ደግሞ 5.4 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ከውጭ የሚላከው ገንዘብ የዓለም ኢኮኖሚ መዋዠቅ ቢኖርም በአንጻራዊነት የተረጋጋ ሆኖ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ የውጭ ሀገር ገንዘብ ዝውውሩ በአብዛኛው ለምርታማ ኢንቨስትመንት ሳይሆን ለቤተሰብ የዕለት ተዕለት ፍጆታ እንደሚውል ሪፖርቱ ጠቅሷል። ከገንዘቡ ውስጥ አብዛኛው ለቤት ኪራይና ግንባታ፣ ለምግብ፣ ለልብስ፣ ለጤና አገልግሎትና ለትምህርት ወጪዎች እንደሚውል አብራርቷል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመደበኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያላቸው እምነት ዝቅተኛ መሆኑ ከውጭ የሚገባው ገንዘብ በባንኮችና በማይክሮፋይናንስ ተቋማት ውስጥ እንደ ቁጠባ እንዳይቀመጥ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ገልጿል።
ይህንን ሁኔታ ለመቀየር የውጭ ምንዛሬ ገበያን ማረጋጋት፣ የገንዘብ ማስተላለፊያ ክፍያዎችን መቀነስ፣ የቁጠባ አማራጮችን ማስፋትና ዲያስፖራው በአገሩ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች እንዲያፈስ አዋጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ማበረታታት እንደሚያስፈልግ ሪፖርቱ መክሯል።
በተለይም የፖለቲካ እምነት ማጣት፣ በፖሊሲዎች ላይ የሚታየው ተደጋጋሚ ለውጥና የንብረት ባለቤትነት መብት ዋስትና አለመኖር በዲያስፖራው ዘንድ እምነትን ከሚያዳክሙ ዋና ዋና ችግሮች መካከል እንደሚገኙ አመልክቷል።
በሌላ በኩል፣ ባለፈው የበጀት ዓመት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የሬሚታንስ መጠን ከቀዳሚው ዓመት በመጨመር 8.2 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል።
Dagu Ethiopia