About
Dagu Ethiopia is an independent newspaper covering Ethiopia: politics, economy, society, culture and more. Our motto is truth, media and society.
How we work Facts first, sources named, and corrections published promptly. Every edition is available in full as a PDF.
Advertising Ads are labelled “Advertisement” and never influence our reporting.
ዳጉ ኢትዮጵያ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበረሰብና ባህል የሚዘግብ ነጻ ጋዜጣ ነው። መሪ ቃላችን እውነት፣ ሚዲያና ማህበረሰብ ነው።
አሠራራችን መጀመሪያ እውነታ፣ ምንጮቻችንን እንጠቅሳለን፣ ስህተቶችንም በፍጥነት እናርማለን። እያንዳንዱ እትም በPDF ሙሉ ይገኛል።
ማስታወቂያ ማስታወቂያዎች “ማስታወቂያ” ተብለው ይሰየማሉ፤ በዘገባችን ላይ ተጽዕኖ የላቸውም።
Add your founding year, editor and team here. / የተመሠረተበትን ዓመት፣ አዘጋጁንና ቡድኑን እዚህ ይጨምሩ።
Contact
Send us tips, corrections, advertising enquiries or feedback. Addis Ababa, Ethiopia.
Address: Bole County 07, H.N 534 Addis Ababa, Ethiopia, 1000
Phone: 911 262 881 704 052 881
Email: info@dagunews.com.et
ጥቆማ፣ እርማት፣ የማስታወቂያ ጥያቄ ወይም አስተያየት ይላኩልን። አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።
አድራሻ፦ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 534 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ 1000
ስልክ፦ 911 262 881 704 052 881
ኢሜይል፦ info@dagunews.com.et
Send message
Privacy policy
Last updated October 23, 2026. Template: review it before relying on it. / ይህ ናሙና ነው፤ ከመጠቀምዎ በፊት ይመርምሩት።
What we collect Only what you send us: your email if you subscribe, and details in messages you write. We do not require accounts.
How we use it To send the editions you asked for and to reply to you. We do not sell your data.
Cookies and ads If we show ads from an ad network, that provider may use cookies to show relevant ads. You can control cookies in your browser.
Your choices Unsubscribe any time, or ask us to delete your data by contacting us.
Other sites and children We link to sites we do not control. Our service is not directed at children.
የምንሰበስበው እርስዎ የሚልኩልንን ብቻ ነው፦ ከተመዘገቡ ኢሜይልዎን፣ እና በመልዕክትዎ ውስጥ የጻፉትን። መለያ (account) አንጠይቅም።
እንዴት እንጠቀምበታለን የጠየቁትን እትም ለመላክና ለመመለስ ነው። መረጃዎን አንሸጥም።
ኩኪዎችና ማስታወቂያ ከማስታወቂያ አውታረ መረብ ማስታወቂያ ካሳየን፣ አቅራቢው ተገቢ ማስታወቂያ ለማሳየት ኩኪዎችን ሊጠቀም ይችላል። ኩኪዎችን በአሳሽዎ መቆጣጠር ይችላሉ።
ምርጫዎ በማንኛውም ጊዜ መውጣት ወይም መረጃዎ እንዲሰረዝ እኛን በማነጋገር መጠየቅ ይችላሉ።
ሌሎች ድረ ገጾችና ልጆች እኛ ወደማንቆጣጠራቸው ድረ ገጾች አገናኝ እናስቀምጣለን። አገልግሎታችን ለልጆች የተዘጋጀ አይደለም።
Back to home
በትግራይ ለሚታቀደው ምርጫ ትብብር እንዲደረግለት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ እዮብ ሀዲስ · 2026-11-24
ኅዳር 16፣ 2019 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ለሚካሄደው ምርጫ ዝግጅት በባለአደራ አስተዳደሩ በኩል የሚያስተባብረው አካል እንዲለይለትና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግለት ጠየቀ።
ቦርዱ ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ለትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር በጻፈው ደብዳቤ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ ምርጫ የማካሄድ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም እንደመሆኑ በክልሉ ለሚታቀደው ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
ምርጫውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ከክልሉ የተለያዩ አካላት ጋር መተባበር እንደሚያስፈልግ ያመለከተው ቦርዱ፣ በዚህ ሂደት የባለአደራ አስተዳደሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝቧል።
በመሆኑም ባለአደራ አስተዳደሩን ወክሎ ከምርጫ ቦርዱ ጋር የሚሠራና ግንኙነት የሚያደርግ አካል በግልጽ እንዲጠቁምለት ጠይቋል። እንዲሁም ለምርጫ ዝግጅት ወደ ክልሉ ለሚላኩ የቦርዱ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር እንዲደረግላቸው አሳስቧል።
ቦርዱ በተጨማሪም የተሽከርካሪ አቅርቦት፣ የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ጽሕፈት ቤቶችን ማደራጀት እንዲሁም ለምርጫ ሥራው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን ማቅረብ ላይ ትብብር ጠይቋል። ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎችም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ አገናኝ አካል እንደሚያስፈልገው ገልጿል።
በጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም. በፌዴራል መንግሥት ይፋ የተደረገው የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከተሰጡት አሥር ዋና ዋና ተግባራት መካከል፣ በስድስት ወራት ውስጥ የተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ በመፍጠር ነፃና ግልጽ ምርጫ ማካሄድ እንዲሁም ክልሉ የፌዴራል ሥርዓቱ መደበኛ አካል እንዲሆን ማስቻል ይገኙበታል።
በሌላ በኩል፣ ለበርካታ ወራት ከመደበኛው ገበያ ጠፍቶ በጥቁር ገበያ ሲሸጥ የቆየው ነዳጅ በመቀሌ ከተማ በነዳጅ ማደያዎች መሸጥ መጀመሩን የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
ነዳጅ ከመደበኛው ገበያ በመጥፋቱ በጥቁር ገበያ የአንድ ሊትር ዋጋ ከ1,000 ብር በላይ ደርሶ እንደነበር ቀደም ሲል መዘገቡ ይታወሳል።
Dagu Ethiopia