About
Dagu Ethiopia is an independent newspaper covering Ethiopia: politics, economy, society, culture and more. Our motto is truth, media and society.
How we work Facts first, sources named, and corrections published promptly. Every edition is available in full as a PDF.
Advertising Ads are labelled “Advertisement” and never influence our reporting.
ዳጉ ኢትዮጵያ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበረሰብና ባህል የሚዘግብ ነጻ ጋዜጣ ነው። መሪ ቃላችን እውነት፣ ሚዲያና ማህበረሰብ ነው።
አሠራራችን መጀመሪያ እውነታ፣ ምንጮቻችንን እንጠቅሳለን፣ ስህተቶችንም በፍጥነት እናርማለን። እያንዳንዱ እትም በPDF ሙሉ ይገኛል።
ማስታወቂያ ማስታወቂያዎች “ማስታወቂያ” ተብለው ይሰየማሉ፤ በዘገባችን ላይ ተጽዕኖ የላቸውም።
Add your founding year, editor and team here. / የተመሠረተበትን ዓመት፣ አዘጋጁንና ቡድኑን እዚህ ይጨምሩ።
Contact
Send us tips, corrections, advertising enquiries or feedback. Addis Ababa, Ethiopia.
Address: Bole County 07, H.N 534 Addis Ababa, Ethiopia, 1000
Phone: 911 262 881 704 052 881
Email: info@dagunews.com.et
ጥቆማ፣ እርማት፣ የማስታወቂያ ጥያቄ ወይም አስተያየት ይላኩልን። አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።
አድራሻ፦ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 534 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ 1000
ስልክ፦ 911 262 881 704 052 881
ኢሜይል፦ info@dagunews.com.et
Send message
Privacy policy
Last updated October 23, 2026. Template: review it before relying on it. / ይህ ናሙና ነው፤ ከመጠቀምዎ በፊት ይመርምሩት።
What we collect Only what you send us: your email if you subscribe, and details in messages you write. We do not require accounts.
How we use it To send the editions you asked for and to reply to you. We do not sell your data.
Cookies and ads If we show ads from an ad network, that provider may use cookies to show relevant ads. You can control cookies in your browser.
Your choices Unsubscribe any time, or ask us to delete your data by contacting us.
Other sites and children We link to sites we do not control. Our service is not directed at children.
የምንሰበስበው እርስዎ የሚልኩልንን ብቻ ነው፦ ከተመዘገቡ ኢሜይልዎን፣ እና በመልዕክትዎ ውስጥ የጻፉትን። መለያ (account) አንጠይቅም።
እንዴት እንጠቀምበታለን የጠየቁትን እትም ለመላክና ለመመለስ ነው። መረጃዎን አንሸጥም።
ኩኪዎችና ማስታወቂያ ከማስታወቂያ አውታረ መረብ ማስታወቂያ ካሳየን፣ አቅራቢው ተገቢ ማስታወቂያ ለማሳየት ኩኪዎችን ሊጠቀም ይችላል። ኩኪዎችን በአሳሽዎ መቆጣጠር ይችላሉ።
ምርጫዎ በማንኛውም ጊዜ መውጣት ወይም መረጃዎ እንዲሰረዝ እኛን በማነጋገር መጠየቅ ይችላሉ።
ሌሎች ድረ ገጾችና ልጆች እኛ ወደማንቆጣጠራቸው ድረ ገጾች አገናኝ እናስቀምጣለን። አገልግሎታችን ለልጆች የተዘጋጀ አይደለም።
Back to home
በሃይማኖት ማንነት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንደ ተራ የጸጥታ ችግር መቁጠር ሀገራዊ ውድቀት ነው ሲል ኢሕአፓ ገለጸ ቴዎድሮስ ክፍሉ · 2026-11-18
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና ተከታዮቿ ላይ እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ፣ የመከፋፈልና የማንነት ማጥፋት መልዕክቶች ከተራ የአመለካከት ልዩነት ያለፉ ከባድ ስጋቶች እንደሆኑ ገለጸ።
ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያን ክርስቲያናዊ ታሪክና ማንነት አፍርሰናል፣ ወደፊትም ይህንኑ ተግባር እንቀጥላለን የሚሉ መልዕክቶችና ዛቻዎች፣ የአንድ ሃይማኖት ተከታዮችን ከመዝለፍ ባለፈ የሀገርን የጋራ ታሪክና ማንነት ለመናድ ያለሙ አደገኛ አካሄዶች ናቸውም ብሏል።
ሌሎችን ሃይማኖቶችና ማንነቶች በማጥፋት የኢትዮጵያ ታሪክ ብቸኛ ባለቤት ለመሆን የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ሊቆም እንደሚገባም ፓርቲው አሳስቧል።
በተጨማሪም በሃይማኖት ማንነት ምክንያት የሚፈጸሙ ግድያዎችንና ጥቃቶችን እንደ ተራ የጸጥታ ችግር መቁጠር ሀገራዊ ውድቀት ነው ብሏል። እንደ ፓርቲው ገለጻ፣ እነዚህ ጥቃቶችና የጥላቻ መልዕክቶች በግልጽ እየተሰራጩና እየተደጋገሙ ሳሉ መንግሥት ዝምታን መምረጡ ከአስተዳደር ድክመት በላይ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነው።
ፓርቲው በመግለጫው፣ ሥልጣን ላይ ያለው አካል በአንድ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በዝምታ የሚመለከት ከሆነ ገለልተኝነቱ አጠያያቂ ይሆናል ብሏል። ይህ ዝምታ ከጥቃቶቹ ጋር ያለው ግንኙነትና ሊኖር የሚችለው ድብቅ ድጋፍ ምን እንደሆነ ጥያቄ እንዲነሳ ያደርጋል ሲልም ጠቅሷል።
በአንድ ቡድን ሃይማኖትና ብሔር ላይ በተደራጀ ሁኔታ የሚፈጸም ጥቃት የዘር ፍጅት ባህሪያትን ሊይዝ እንደሚችል ያነሳው ኢሕአፓ፣ በኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ነው የሚላቸው መሰል ጥቃቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩ ጥሪ አቅርቧል።
ፓርቲው በመጨረሻም፣ ማንም የሌላውን ሃይማኖት ወይም ታሪካዊ ማንነት በማፍረስ የሀገር ታሪክ ብቸኛ ባለቤት ለመሆን መሞከር እንደማይገባው በማስገንዘብ፣ ለሚፈጸሙ ጥቃቶችና ለተሰራጩ የጥላቻ መልዕክቶች ገለልተኛና ግልጽ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።
Dagu Ethiopia