About
Dagu Ethiopia is an independent newspaper covering Ethiopia: politics, economy, society, culture and more. Our motto is truth, media and society.
How we work Facts first, sources named, and corrections published promptly. Every edition is available in full as a PDF.
Advertising Ads are labelled “Advertisement” and never influence our reporting.
ዳጉ ኢትዮጵያ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበረሰብና ባህል የሚዘግብ ነጻ ጋዜጣ ነው። መሪ ቃላችን እውነት፣ ሚዲያና ማህበረሰብ ነው።
አሠራራችን መጀመሪያ እውነታ፣ ምንጮቻችንን እንጠቅሳለን፣ ስህተቶችንም በፍጥነት እናርማለን። እያንዳንዱ እትም በPDF ሙሉ ይገኛል።
ማስታወቂያ ማስታወቂያዎች “ማስታወቂያ” ተብለው ይሰየማሉ፤ በዘገባችን ላይ ተጽዕኖ የላቸውም።
Add your founding year, editor and team here. / የተመሠረተበትን ዓመት፣ አዘጋጁንና ቡድኑን እዚህ ይጨምሩ።
Contact
Send us tips, corrections, advertising enquiries or feedback. Addis Ababa, Ethiopia.
Address: Bole County 07, H.N 534 Addis Ababa, Ethiopia, 1000
Phone: 911 262 881 704 052 881
Email: info@dagunews.com.et
ጥቆማ፣ እርማት፣ የማስታወቂያ ጥያቄ ወይም አስተያየት ይላኩልን። አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።
አድራሻ፦ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 534 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ 1000
ስልክ፦ 911 262 881 704 052 881
ኢሜይል፦ info@dagunews.com.et
Send message
Privacy policy
Last updated October 23, 2026. Template: review it before relying on it. / ይህ ናሙና ነው፤ ከመጠቀምዎ በፊት ይመርምሩት።
What we collect Only what you send us: your email if you subscribe, and details in messages you write. We do not require accounts.
How we use it To send the editions you asked for and to reply to you. We do not sell your data.
Cookies and ads If we show ads from an ad network, that provider may use cookies to show relevant ads. You can control cookies in your browser.
Your choices Unsubscribe any time, or ask us to delete your data by contacting us.
Other sites and children We link to sites we do not control. Our service is not directed at children.
የምንሰበስበው እርስዎ የሚልኩልንን ብቻ ነው፦ ከተመዘገቡ ኢሜይልዎን፣ እና በመልዕክትዎ ውስጥ የጻፉትን። መለያ (account) አንጠይቅም።
እንዴት እንጠቀምበታለን የጠየቁትን እትም ለመላክና ለመመለስ ነው። መረጃዎን አንሸጥም።
ኩኪዎችና ማስታወቂያ ከማስታወቂያ አውታረ መረብ ማስታወቂያ ካሳየን፣ አቅራቢው ተገቢ ማስታወቂያ ለማሳየት ኩኪዎችን ሊጠቀም ይችላል። ኩኪዎችን በአሳሽዎ መቆጣጠር ይችላሉ።
ምርጫዎ በማንኛውም ጊዜ መውጣት ወይም መረጃዎ እንዲሰረዝ እኛን በማነጋገር መጠየቅ ይችላሉ።
ሌሎች ድረ ገጾችና ልጆች እኛ ወደማንቆጣጠራቸው ድረ ገጾች አገናኝ እናስቀምጣለን። አገልግሎታችን ለልጆች የተዘጋጀ አይደለም።
Back to home
የቴዲ አፍሮ ወዳጅ የስምንት ወራት እስር፦ የዋስትና እምቢታውና የክሱ አነጋጋሪ ገጽታዎች ሀና ሰለሞን · 2026-11-10
አዲስ አበባ: ስምንት ወር ሙሉ የቴዲ አፍሮ ጓደኛ እስር ቤት ነው። የቴዲ አፍሮ ጓደኛ ብቻ ሆኖ ሳለ የቴዲ አፍሮ ኦፊስ ማናጀር ነው በሚል አቃቤ ህግ ክስ ላይ ማስገባቱ እጅግ አነጋጋሪ ሆኗል፣ ጥያቄንም ፈጥሯል።
ቴዲ አፍሮ 'ኢትዮ ሪካ' የሚል መጠሪያ ያለው አልበሙን ማውጣቱን ተከትሎ ከድምጻዊው ጋር በቅርብ ጓደኝነት የሚታወቀውና ላለፉት ስምንት ወራት በእስር ላይ የሚገኘው የሱፍ ያሲን የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ውድቅ መደረጉ አነጋጋሪ ሆኗል። ተከሳሹ በተከሳሽነት ጉዳይ በተለያዩ የፍርድ ቤት እርከኖች ዋስትና ጠይቆ፣ የመጨረሻ ተስፋው በነበረውና አምስት ዳኞች በተሰየሙበት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ባለፈው ሐሙስ የዋስትና መብቱ ውድቅ አድርጎበታል። በመሆኑም ተከሳሹ ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ተወስኗል።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሕግ ባለሞያዎችና በታዛቢዎች ዘንድ በርካታ የህግና የሎጂክ ጥያቄዎችን አስነስቷል። ያነጋገርናቸው የህግ ባለሞያዎች በሙያዊ ምልከታቸው እንደሚያስገነዘቡት የሱፍ የተጠረጠረበት ጉዳይ በህግ አግባብ የዋስትና መብትን በሙሉነት የሚያስከክል አይደለም። የዋስትና መብት ህገመንግስታዊ መብት ሆኖ ሳለ ጉዳዩ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ተከሳሹ በእስር እንዲቆይ መደረጉ የፍትህ ስርዓቱን ንጽህና ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው።
ከዚህም ባሻገር በክስ መዝገቡ ላይ የቴዲ አፍሮ ኦፊስ ማናጀር ወይም የቢሮ ሃላፊ ተብሎ መጠቀሱ ታዛቢዎችን ክፉኛ አስገርሟል። በእውነታው ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ሥራውን የሚያከናውነው የቢሮ ሃላፊ መድቦ ባለመሆኑና እንዲህ አይነት መዋቅርም ስለማያስፈልገው፣ ተከሳሹ የድምጻዊው ጓደኛ እንጂ ማናጀሩ አይደለም። የህግ ሰዎች ይህንን ውስጠ ነጥብ አቃቤ ህግ የጓደኛን ስም ወደ ኦፊስ ማናጀርነት በመቀየር የክሱን ክብደት በህዝብ ዘንድ ለማሳደግ አለያም ጉዳዩን ከግለሰብ ክስ ይልቅ ከተዋቂው ድምጻዊ ሥም ጋር በማያያዝ ለማስተሳሰር ሆን ተብሎ የተደረገ ስልት ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።
ከህጋዊ ሂደት ይልቅ የጉዳዩ ሰብአዊ ገጽታ እጅግ ልብ ሰባሪ ነው። ተከሳሹ ገና በቅርቡ ከፎቅ ላይ ወድቆ ህይወትን ያጣውን ህፃን ልጁን ሀዘን በቅጡ ሳይወጣ በማረሚያ ቤት ውስጥ የስነ ልቦና እና የአካል ስቃይ እያሳለፈ ይገኛል። ፍርድ ቤቱ ይህን ጥልቅ ሰብዓዊ ቀውስ እና ቤተሰባዊ ሀዘን ከግምት ውስጥ አለማስገባቱም የፍትህ ስርዓቱ ሊኖረው የሚገባውን ርህራሄ እና ሰብዓዊነት ያሳጣው ሆኗል።
በችሎቱ ውሳኔ መሰረት አቃቤ ህግ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ በእስር ላይ ያሉ ምስክሮችን ማቅረብ እንዲጀምር ትእዛዝ ተሰጥቷል። ይሁን እንጂ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች እንደገለጹት አቃቤ ህግ በተቀጠረበት ዕለት ምስክሮችን አሟልቶ ያቀርባል ብለው አያምኑም። ይልቁንም "ምስክሮችን እያፈላለኩ ነው፣ አልተገኙም፣ መጥሪያ አልደረሳቸውም የሚሉ የስነ ስርዓት ምክንያቶችን በመደርደር ተጨማሪ ጊዜ ለመግዛትና የተከሳሹን የእስር ቆይታ ለማራዘም የሚደረግ የህግ ስልት ሊጠቀም እንደሚችል ይታሰባል።
አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የህግ ባለሙያ ለዳጉ ኢትዮጵያ ሲናገሩም 'በህግ ዋስትና ሊያገኝ የሚችል ክስ ሆኖ ሳለ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ መብቱ መከለከሉን እንዲሁም ተከሳሹ የድምጻዊ ጓደኛ ብቻ ሆኖ ሳለ ማስረጃ በሌለ ሁኔታም የቴዲ አፍሮ ኦፊስ ማናጀር በመባል መፈረጁ' ጉዳዩ ከንጹህ የህግ ጥሰት ይልቅ የተለየ ፍላጎት ሰለባ መሆኑን ስጋት ይፈጥራል ብለዋል። አቃቤ ህግ ዛሬ ማክሰኞ በሚኖረው የችሎት ላይ ምስክሮችን በአግባቡ የማያቀርብ ከሆነ እስሩ ፍትህ ለማስፈን ሳይሆን ቅጣትን በቅድሚያ ማስተላለፍ (punishment by process) ታስቦ የተደረገ መሆኑን ይበልጥ ያጋልጣል።" ሲሉም አክለዋል።
Dagu Ethiopia